About this podcast
ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላዉ ዓለም የተደረጉ፣ ሊደረጉ የታቀዱና የተነገሩ ዓበይት ፖለቲካዊ ጉዳዮች ዘወትር ሰኞ ይቃኙበታል። ዝግጅቱ የሐገራትን፣ የዓለም አቀፍ እና አካባቢያዊ ማሕበራትን፣ድርጅቶችንና የታዋቂ ግለሰቦችን ያለፈ፣ያሁንና የወደፊት ምግባሮችን እያነሳ በባለሙያዎች አስተያየት የተደገፈ ትንታኔ ይቀርብበታል። አዘጋጅ፣ ነጋሽ መሐመድ
Episodes
The newest 20 of 100 episodes
- ማሕደረ ዜና፣ የሁቲዎች ድል፣ ያልተጠበቀዉ መራር ዕዉነት · 13 minየዓለምን ሠላም ያስከብራል የተባለዉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ከተፋላሚዎች አንዱን ምናልባትም የዓለም ገዢዎችን አገዛዝ የሚቃረነዉን ግን በኢራን የሚደገፈዉን አንሳር አላሕን ከመወንጀል-መቅጣት ባለፍ ጦርነት-ግጭቱን ለማስቆም እስካሁን የተከረዉ የለም
- ማሕደረ ዜና፣ የዲሞክራቶች ድል የትራምፕን መርሕ ይቀይር ይሆን · 14 minትራምና ኔታንያሁ የጫሩት እሳትና አፀፋዉ ኢራንን፣ሊባኖስን፣የመንን፣እስራኤልን፣ ከኢራቅ እስከ ኩዌት የሚደርሱ የፋርስ ባሕረ ሠላጤ ሐገራትን ክፉኛ ጎድቷል።ኢራኖችን ግን ዛሬም አልተሸነፉም።ጥቅምት 29 ቀን 2026 እስራኤል፣ በአራተኛ ቀኑ ዩናይትድ ስቴትስ ላይ በተደረገዉ ምርጫ ግን…
- ማሕደረ ዜና፥ ኢትዮጵያ፣ ሸቀጥ የተወደደ፣ ሞት የረከሰባት ሐገር · 13 minኢትዮጵያ ዉስጥ ለሰዎች በጣሙን ለየዋሆች ሕይወት የሚጨነቅ አይደለም የሚያሳብ ፖለቲከኛ መገኘቱ እያጠራጠረ ነዉ።ወይም አስከሬን መቅበር፣ ተፈናቃይ መቁጠር፣ ለየጦርነት ግጭቱ «ጠላት» የሚባሉ ወገኖችን ማሳጣት፣ ሰበብ ምክንያት መደርደሩ ተለመደና አስጨናቂዉ ጥፋት የወትሮ ምግባር የሆነ…
- የፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መንግሥት ውጥረት ውስጥ የገቡትን የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ባለሥልጣናት በሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ማገናኘት ይፈልጋል · 12 minኃይለኛ ፍጥጫ ውስጥ ለገቡት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ባለሥልጣናት የፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን መንግሥት በዚህ ሣምንት በሚካሔደው የሩሲያ አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ የመገናኛ መድረክ መፍጠር ይፈልጋል። ግብጽ በቀይ ባሕር በኩል ኢትዮጵያ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገው ግፊት እና…
- ማሕደረ ዜና፣ ቀይ ባሕር፤ በደም ቀልቶ ደም የሚገበርለት ባሕር · 14 minኢትዮጵያና ኤርትራ አንድ ሐገር በነበሩበት ዘመን ይዋጉ ነበር።30 ዓመት። ሁለት ሐገርም ሆነዉ ይዋጋሉ።የአሥመራና የአዲስ አበባ መሪዎች ያልተዋጉበት ጊዜ ከነበረ-አንድም-በ1990ዎቹ እንዳየነዉ «የጋራ ጠላት» የሚሏቸዉን መንግሥትን ወይም በ2013 እንደሆነዉ የመቀሌ ገዢዎችን…
- ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ጦርነት፣ የኢትዮ-ኤርትራ ፍጥጫ መቆሚያዉ መቼ ነዉ? · 15 minየኢትዮጵያና የኤርትራ መንግሥታት ጠብ በናረበት በዚሕ ወቅት የኢትዮጵያ የሥለላ መስሪያ ቤት ኃላፊ፣ሌሎች ባለሥልጣናት፣ የጦር ጄኔራሎችና የተባባሪዎቹ ኃይላት የጦር አዛዦች ሥልታዊቱን ከተማን አዲግራትን የመጎብኘታቸዉ ፖለቲካዊ መልዕክት ከደብረፂዮን እኩል ለኢሳያስ አፈወርቂ መሆኑ…
- ማሕደረ ዜና፣ የኢትዮጵያ ጦር መቀሌን ተቆጣጠረ፣ጦርነቱ አላባራም፣አካባቢያዊዉን ማስጋቱም ቀጥሏል · 14 minከየካቲት 1981 ጀምሮ መቀሌ ከህወሓት እጅ ስትወጣ ያሁኑ ሁለተኛዋ ነዉ።የመጀመሪያዉ የፌደራሉ መንግሥት ህዳር 2013 ከተማይቱን ሲቆጣጠር ነበር።ግን ከሰባት ወር በላይ አልቆየም።ህወሓት መልሶ ተቆጣጠራት።ዘንድሮም ከመቀሌ ድል-ሽንፈት በኋላ ጦርነቱ ቦታ-ይቀይር እንጂ አላባራም
- ማሕደረ ዜና፣ ኢትዮጵያ የጦርነት ማግሥት አዲስ ጦርነት መፍለቂያ ምድር · 15 minጦርነት ሲጀመር «ተፋላሚዎች መጀመሪያ የሚገድሉት ዕዉነትን ነዉ» እንዲሉ ሆኖ የጦርነቱ ጀማሪ ማንነትን መለየት፣ እስካሁን የተገደለና የሞተዉን ሰዉ ቁጥር በዝርዝር ማወቅ አይቻልም።ተፋላሚ ኃይላት፣ ደጋፊዎቻዉ፣ መገናኛ ዘዴዎቻቸዉና በየፊናቸዉ ያደራጁት የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች…
- ሑቲዎች እና ሳዑዲ አረቢያ የገጠሙት ጦርነት በደሐዋ የመን ሲቪሎችን ወደ ሰቆቃ እየገፋ ነው · 13 minየአንሳር አላሕ ንቅናቄ ከጅቡቲ 20 ኪሎ ሜትር ገደማ የምትርቀውን ማዩን ወይም ፔሪም ደሴት እና ኤርትራ ከየመን የተዋጋችባቸው የሐኒሽ ደሴቶችን ጨምሮ ከቀይ ባሕር ዳርቻ የሚገኘውን ምዕራባዊ የመን ለመቆጣጠር የፈጀበት ሣምንት ገደማ ብቻ ነው። በውጊያው ቱርክ እና ፓኪስታን ሳዑዲ…
- ማሕደረ ዜና፣ የመስከረም 11፣ 2001 ጥቃት ዝክር-«ጦርነቱ ይቀጥላል» ትራምፕ · 14 minጥቃቱ ሲፈፀም ፕሬዝደንት ጆርጅ ቡሽ ሳራሶታ፣ ፍሎሪዳ የአንድ ትምሕርት ቤት ተማሪዎችን እያነጋገሩ ነበር።ፕሬዝደንቱ ከመሩት የመልዕክተኞች ጓድ ጋር አብሮ የተጓዘዉ ጋዜጠኛ ስቲቭ ሆላንድ እንደሚያስታዉሰዉ ቡሽ ከኒዮርኩ ሕንፃዎች የመጀመሪያዉ መመታቱን ሲሰሙ «የፓይለት ስሕተት ነዉ»…
- ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የእስራኤል መሪዎች የጫሩት ጦርነት 6ኛ ወር · 15 minበጣም ከረዘመ በሥድት ሳምንት የቴሕራን ሥርዓትን መነቃቅሮ ለመጣል፣ የኑክሌር መርሐ-ግብሯን ለመረከብና የአሜሪካ ታማኝ ሥርዓት ቴሕራን ላይ ለመትከል የዋሽግተን-ቴል አቪቭ መሪዎች ለየሕዝባቸዉ የገቡት ቃል ግን በርግጥ በንኗል
- ማሕደረ ዜና፣ የ4 ዓመታት ዝግጅት፣የ40 ቀናት ጉባኤ-ለኢትዮጵያ ይበጅ ይሆን? · 22 minባለፈዉ ሳምንት ማብቂያ በተጠናቀቀዉ ምክክርም ህወሓትን ይዞ፣ ፋኖን፣ ኦነሠን፣ የበኒ ሻንጉል-ጉሙዝ፣ የጋምቤላ ክልሎች አማፂያንን አክሎ፣ ገሚስ-ኦብነግን፣ እንደ ኦነግ፣ ኦፌኮ የመሳሰሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፣ ከሐገር ዉጪ የሚገኙ የፖለቲካ፣ የአካባቢ፣ የመብት ተሟጋቻች ማሕበራትን ጨምሮ…
- ማሕደረ ዜና፣ የትራምፕ እብሪት፣ በፍርሐት የተጠፈነገዉ ዓለምና የአፍሪቃ ፈተና · 15 minየሆርሙዝ ወሽመጥ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ መዘጋቱ በተለይ አፍሪቃ በማታዉቀዉ፣በማያገባትና በማትፈልገዉ ጦርነት የርዳታ ተመፅዋች ዜጎችዋን ሕይወት እንድትከፍል አስገድዷታል።ከኢትዮጵያ እስከ ናጄሪያ፣ ከሶማሊያ እስከ ሴኔጋል የሚገኙ የአፍሪቃ ሐገራት የርዳታ እሕል፣ መድሐኒት፣ቁሳቁስ…
- ማሕደረ ዜና፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት፣ የኃይል አሰላለፉ እንዴትነት፣ ምክንያትና መዘዙ · 13 minአፍሪቃ «የራስዋን ችግር በራስዋ መፍታት የመቻሏ» አብነት፣ ኢትዮጵያዉያን እንደሚዋጉት ሁሉ «ለሰላማዊ ዉል ለመገዛትም ፈቃደኛ የመሆናቸዉ» ምሳሌ ተደርጎ ብዙ የተነገረለት የፕሪቶሪያ ሥምምነት ተኩስ ከማስቆሙ እኩል የአዲስ የኃይል አሰላለፍ ምክንያት መሆኑ ነዉ ዚቁ።የተፋላሚ ኃይላት…
- ማሕደረ ዜና፣ የሸረሪና ዉጊያ፣ «የክተት» አዋጅና የፕሪቶሪያ ዉል · 13 minከሰኔ 30 በኋላ ከህወሐት ያፈነገጠዉ አንጃ አዲስ አበባ ዉስጥ የትግራይ ተወላጆችና ደጋፊዎቻቸዉን «ጦርነት አንፈልግም» በሚል በአደባባይ ሲያሰልፍ፣ መቀሌ ዉስጥ ደግሞ ህወሓት የጠራዉ ተቃራኒ ህዝባዊ ሥብሰባ ተደርጓል።ስልፍና ስብሰባዉ የቃላት ጦርነቱን ወደየደጋፊዎቻቸዉ ለማስረፅ…
- ማሕደረ ዜና፣ የአሜሪካና የኢራን ጦርነት-አዳዲሶቹ የጦር ግንባሮች · 14 minየዩናይትድ ስቴትስና የእስራኤል መሪዎች፣ የቴሕራኖችን ማስጠንቀቂያ ንቀዉ፣ የዲፕሎማት፣ ተንታኖችን ምክር-ማሳሰቢያ አጣጥለዉ የካቲት 28፣ 2026 ኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት በስድስተኛ ወሩ ሁለተኛ የዉጊያ ግንባር አስከፈተ። የባብ ኤል መንደብ ወሽመጥን አዘጋም።ሥልታዊዉ ወሽመጥ…
- ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዉሳኔ፣የሶማሊያ ሠላምና የአፍሪቃ ሕብረት ተልዕኮ የመጨረሻ መጀመሪያ · 14 minየአሜሪካ ዉሳኔ ከአዉሮጳ ሕብረትና ከፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ዉሳኔዎች ጋር መቃረኑ ዋሽግተኖች ለዉሳኔዉ የሰጡትን ምክንያት አጠያያቂ አድርጎታል።አጠያየቀም-አላጠያየቀ የአሜሪካ ዉሳኔ የአፍሪቃ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ ብዙዎች እንደሚሉት 20 ዓመት ግድም ላስቆጠረዉ ለአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት…
- የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ማን ወደ ድርድር ይመልሳቸዋል? · 11 minየአዲስ አበባና የመቐለ ባለሥልጣናት ለመወያየት ፍላጎት እንዳላቸው ፍንጭ ቢሰጡም በመካከላቸው ያለው እሰጥ አገባ ከፍተኛ ዕልቂትና ብርቱ ውድመት ያስከተለው ጦርነት እንዳያገረሽ የሚያሠጋ ነው። በጥቅምት 2013 ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የኢትዮጵያ ፌድራል መንግሥትና ህወሓትን ወደ…
- ማሕደረ ዜና፣ የዩናይትድ ስቴትስ ነፃነት 250ኛ ዓመት ዝክርና ዉዝግብ · 15 minከዓለም ምጣኔ ሐብት 23 ከመቶዉን ያክል የምትቆጣጠረዉ ዩናይትድ ስቴትስ ናት።ከ31 ትሪሊዮን ዶላር በላይ።ዩናይትድ ስቴትስን በሩቅ ርቀት የምትከተለዉ ቻይና፣ ቻይናን እጅግ በጣም ርቃ የምትከተለዉ ጀርመንና ከጀርመን የምትቀጥለዉ የጃፓን ኤኮኖሚ ቢደመር የአሜሪካንን…



